Search

ታሪካዊ ዳራ

ፍትሕ ሚኒስቴር አሁን ያለውን ስያሜ ከመያዙ በፊት የተለያዩ መጠሪያዎችን በመያዝ አወቃቀሩም ሆነ አደረጃጀቱ በየጊዜው ለውጦች ሲካሄዱበት መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ተቋሙ በተለያዩ ጊዜያት የሚኖረው አደረጃጀት ያለፈባቸውን ሥርዓተ ማህበራትና ቅርፀ መንግስታት አሠራርና ይዘት በሚያንፀባርቅ መልኩ የተደራጀ ሲሆን ይህም በተለይ ከዳኝነት ሥርዓቱ ጋር እስከ ቅርብ ጊዜያት የነበረው ቁርኝት ለዚህ አመላካች ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

ስለሆነም ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርነው ሁሉ ይህ ፅሁፍ የፍትሕ ሚኒስቴር ከየት ተነስቶ አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደቻለ፣በየወቅቱ ሲከተላቸው  የነበሩ አሠራሮች ምን እንደሆኑ፣እንዲሁም አሁን ያለው አወቃቀርና የደረሰበት ደረጃ  ከዚህ ቀጥሎ ለማየት እንሞክራለን፡፡

. ፍትሕ ሚኒስቴር እስከ ደርግ ውድቀት

የፍትሕ ሚኒስቴር በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመው በአፄ ሚኒሊክ ዘመነ-መንግስት ሲሆን ጊዜውም ጥቅምት 15 ቀን 1900 . ነው፡፡ በወቅቱም 12 የተለያዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የተቋቋሙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የዳኝነት ሚኒስቴር ነበር፡፡ በወቅቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የአገር ዳኞች ዋና አለቃ ፣የሚፈርደውን ፍርድ ሁሉ በፍትሐ-ነገስት[1] ቃል በትጋት የሚጠብቅ ፣የሚፈርደውንና ባገር ውስጥ የሚፈረደውን ፍርድ ሁሉ በመዝገብ የሚፅፍ መሆኑን የሚሉት ተግባርና ኃላፊነት የተሰጡት መሆኑን በዝክረ ነገር ገፅ 68 ላይ በግልፅ ሰፍሮ ይገኛል ፡፡

ከዚህ በኋላ በተደረገው ለውጥ ማለትም 1914 አካባቢ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የዳኝነት ሚኒስቴር መባሉ ቀርቶ የፍርድ ሚኒስቴር በሚል ስያሜ እንዲጠራ የተደረገው ሲሆን በዚህ የፍርድ ሚኒስቴርነት ሥልጣኑ የፍርድ ሥራ አካሄዱን ይመራ እንደነበር የተለያዩ ፅሁፎች ያስረዳሉ፡፡ ከዚህም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ማቋቋሚያ አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው የዳኝነት ሥርዓቱም ሆነ የፍርድ ሁኔታው በእጅጉ በነገስታቱ መልካም ፈቃድ ላይ መሠረቱን የጣለ ነበር፡፡

በመቀጠል በሥልጣን ላይ የወጣው የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግስትም ቢሆን ቀደም ሲል ከነበረው ብዙም የተለየ አልነበረም፡፡ በዚህ ወቅት በዋናነት ትኩረት የተሰጠው የኢትዮጵያን የተማከለና ጠንካራ የአስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት ዓላማ ያደረገ ሲሆን ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል የዳኝነት ሥርዓቱን እንደገና ለማደራጀት የተወሰደው ሲሆን ለዚህም አጋዥ የሆኑ ሕግጋት ወጥተው በሥራ ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፡፡ ከዚህ አንፃር የዳኝነት ሥራ አካሄድን በሚመለከት አዋጅ ቁጥር 2/1934 እና አዋጅ ቁጥር 29/1934 ወጥተው በሥራ ላይ ውለዋል፡፡ በእነዚህም የሕግ ድንጋጌዎች መሠረትም በወቅቱ የነበረው የፍርድ ሚኒስቴር ፍርድ ቤቶችንና የዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤትን በአንድ ላይ ሲያስተዳድር ቆይቷል፡፡

በቀጣይ ስለሚኒስትሮች ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው ትዕዛዝ ቁጥር 1/1935 ስያሜው ባይለወጥም ሥልጣንና ተግባሩ ተለይቶ በአዲስ መልክ እንዲቋቋም የተደረገ ሲሆን በዚህ ትዕዛዝ መሠረት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አግባብ ያላቸው ዳኞችን አቅርቦ በንጉሱ እንዲሾሙ የማድረግ፣አስፈላጊ ሲሆን ተጨማሪ ፍርድ ቤቶችን የማቋቋም፣የፍርድ ሥራን እንዲከናወን የማድረግ፣የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሠዎችንም ላይ ሆነ የምህረት ጥያቄ ላይ የራሱን ኃሳብና አስተያየት በመጨመር ለንጉሠ ነገሥቱ የማቅረብ፣ ለጠበቆች የሥራ ፈቃድ የመስጠት እንዲሁም የሕግ ኃሳቦችን አሰናድቶ የማቅረብ ሥልጣን ተሰጥተውት ነበር ፡፡ ይህም ከቀድሞው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሥልጣን ለየት የሚያደረገው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሕግ ተርጓሚውን ሥራ ከመምራት ባለፈ ራሱ ዳኛ ሆኖ እንዳይሰራ መሆኑ ሲሆን ይህም በተወሰነ መልኩ የሥራ ክፍፍል መጀመሩን አመላካች ነበር፡፡ ያም ቢሆን ግን የዳኝነት አካሉ ሙሉ በሙሉ ከተፅዕኖ ነፃ ያልነበረ መሆኑን ለመረዳት ይቻላል፡፡

በእነዚህ ጊዜያት ዐቃቤ ሕግ በፍርድ ቤቶች ዘንድ ለሚቀርቡ ነገሮች ሕግን የሚያስከብር ጠበቃ ሲሆን ሥራውም በጠቅላላ የሕዝብን ፀጥታ የሚነኩትን ሕጎች እንዲከበሩ ማድረግ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር እስከ 1954 / ማለትም የወ////ሕግ እስኪወጣ ድረስ/ በክስ አቤቱታ አቅራቢነት ከሚያስቀጡ ወንጀሎች በቀር በማናቸውም የወንጀል ጉዳይ መንግስትን ወክሎ በመከራከር ወንጀል የፈፀሙ ሰዎች ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ በሌላ በኩል የፍትሐብሔር ጉዳዮችን ከመከታተል አንፃር ለዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት የተሰጠው የሥራ ድርሻ የሌለ ሲሆን 1952 የፍትሐብሔር ሕግን መውጣት ተከትሎ ግን

-በሕጉ በክብር መዝገብ አፃፃፍ ላይ ስህተቶች ሲኖሩ እንዲታረሙ የማድረግ  ( አንቀፅ 122)
-
አካለ መጠን ያላደረሰም ሆነ በፍርድ ቤት ውሳኔ የተከለከለ ሠው አሳዳሪ ወይም ሞግዚት እንዲሻር ለፍርድ አቤቱታ የማቅረብ( ቁጥር 234 ላይ እንደሰፈረው)
-
ዕብድ ወይም ድውይ የሆነ ሠው እንዲከለከል ተገቢው አቤቱታ ለዳኞች የማቅረብ( በቁጥር 353/1/
-
ዕብድ ወይም ድውይን በሚመለከት በዳኞች የተሠጠ የክልከላ ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ አቅርቦ ይግባኝ ሰሚው /ቤት በሥር /ቤት የተሰጠውን የክልከላ ውሳኔውን እንዲያሻሽልለት ወይም እንዲሽርለት ተገቢውን አቤቱታ የማቅረብ( ቁጥር 355 እና 377/1/ ላይ እንደተደነገገው)
-
በሕግ የተከለከለ ሠው ከሥልጣኑ በላይ የሆነ ሕጋዊ ተግባር ፈፅሞ ሲገኝ ተግባሩ ያስከተለው ሕጋዊ ውጤት ፈራሽ እንዲሆን ለፍርድ ቤት አቤቱታ የማቅረብ ኃላፊነት( ቁጥር 387/2/ ላይ እንደሰፈረው)
-
ሕገ ወጥ የሆነ ጋብቻ እንዲፈርስ ለፍርድ ቤት አቤቱታ የማቅረብ( ቁጥር 592/2/ እንደተደነገገው) የሚሉት ኃላፊነቶች ተሰጥተውታል፡፡ 

በተመሳሳይ 1952 በታወጀው የኢትዮጵያ ንግድ ሕግ ቁጥር 975// በተደነገገው መሠረት የነጋዴ መክሰር እንዲወሰን ተገቢውን አቤቱታ የማቅረብ ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ 1954 የወ////ሕጉን መውጣት ተከትሎም የዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት ቀደም ሲል በወንጀል ጉዳዮች ላይ የነበረው የሥራ ድርሻ እንዲሰፋ ተደርጎ በክስ አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስቀጡ ወንጀሎችንም የማየት ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡  

የንጉሱ ሥርዓት አብቅቶ በምትኩ ወታደራዊ ደርግ በትረ ሥልጣኑን ቢይዝም ቀደም ሲል ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተሰጠው ስያሜ እንዳለ እንዲቀጥል የተደረገ ሲሆን በጥቅምት ወር 1968 በተላለፈ መመሪያ የሕግና የፍትሕ ሚኒስቴር በሚል ሥያሜ እንዲተካ ተደርጓል፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ይህንኑ ስያሜ በመያዝ በአዋጅ ቁጥር 127/69 የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት ሲወጣ ቆይቷል፡፡ [2] ይህ አዋጅም እስከ 1979 መጨረሻ ድረስ ፍርድ ቤቶችንና የዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤቶችን በሚኒስትሩ ሥር ሆነው እንዲቆዩ አድርጓል፡፡

1980 . የኢሕዲሪ መንግስት ምስረታን ተከትሎ በወጣው አዋጅ ቁጥር 8/1980 ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሲጠራበት የነበረውን የሕግና የፍትሕ ሚኒስቴር በፍትሕ ሚኒስቴር እንዲተካ የተደረገ ሲሆን በዚሁ አደረጃጀት መሠረትም ቀደም ሲል በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሥር የነበሩት ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለየብቻቸው ራሳቸውን ችለው እንደወጡ ተደርጎ ከፍተኛና አውራጃ ፍርድ ቤቶች ግን በፍትሕ ሚኒስቴር ሥር ሆነው እንዲቀጥሉ  ተደርጓል፡፡         

. ፍትሕ ሚኒስቴር ከደርግ ውድቀት በኋላ

ከደርግ ውድቀት በኋላ የተቋቋመው የሽግግር መንግስት የፍትሕ አስተዳደሩን አስመልክቶ ገንቢ የሆኑ እርምጃዎች የወሰደ ሲሆን ከዚህ አንፃር የዳኝነት አካሉ ከአስፈፃሚው አካል ነፃ ሆኖ እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ በዚሁም መሠረት በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ያለውን የፌዴራል አወቃቀር መሰረት በማድረግ ፍርድ ቤቶች የማዕከላዊ መንግስት እና የክልል ፍርድ ቤቶች በኋላም የፌዴራል መንግስት እና የክልል ፍርድ ቤቶች በሚል በአዋጅ ተቀቁመውና ሕገ መንግስታዊ እውቅና ተሰጥቷቸው እንዲዋቀሩ ተደርጓል፡፡

ከዚህ አኳያ የፍትሕ ሚኒስቴርም ከፍርድ ቤቶች ተለይቶ በአዋጅ ቁጥር 4/1987 መሠረት እንዲቋቋም የተደረገ ሲሆን ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነቱ በአዋጁ በአንቀፅ 23 ላይ ሰፍሮ ይህንኑ ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በመቀጠል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የኢፌዲሪ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 471/98 መሠረት ተሻሽሎ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ሲያከናውን የቆየ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የኢፌዲሪ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 691/2003 መሠረት ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በአዋጁ አንቀፅ 16 የተሰጡትን ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት እና በአንቀፅ 10 ላይ የተሰጡትን የወል ሥልጣንና ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡የፌዴራል  ጠቅላይ  ዐቃቤ  ህግ ራዕይ፣ ተልዕኮና  እሴቶች  

 እስትራቴጂስ • በፌደራል ፍርድ ቤቶች ሥልጣን ሥር የሚወድቅ ወንጀል ተፈፅሟል ብሎ ሲያምን ምርመራ እንዲካሄድ ያደርጋል፤ በቂ ምክንያት ሲኖር የተጀመረውን ምርመራ ያቋርጣል ወይም ተጨማሪ ምርመራ የከናውናል፤ • የፌደራል መንግስትን በመወከል የወንጀል ክስ ይመሰርታል፤ ይከራከራል፤ በቂ ምክንያት ሲኖር በሕጋ መሰረት ክሱን ያነሳል፤ ፍርድ ቤቶች የሚሰጧቸውን ውሣኔዎች መፈፀማውን የከታተላል፤ • የወንጀል ፍተሕ መረጃዎች አሰባሰብ፤ አያያዝና ስርጭት ሥርዓት ይዘረጋል፤ ለሚመለከታቸው የፍትሕ አካላት ድጋፍ ይሰጣል፤ • የመንግስት መ/ቤቶችንና የልማት ድርጅቶቹን የፍርድ ባለመብት ያደረጉ የፍርድ ቤት ውሳኔዎችም እዲፈፀሙ መደረጋቸውን ይከታተላል፤ • የፌደራል መንግሥት መ/ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ተከራካሪ የሚሆኑባቸው የፍተሐብሄር ክሶችና የመብት ጥያቄዎች አያያዝን ይከታተላል፤ ሪፖርት እንዲቀርብለት ያደርጋል፤ ብቃት ያለው የሕግ ባለሙያ መመደቡን ያረጋገጣል፤ የሕጋ ጥሰት አለ ብሎ ሲያምን የእርምት መመሪያ ይሰጣል ተፈፃሚነቱንም ይከታተላል፤ • የፌደራ መንግስት መ/ቤቶችና የልማት ድርጅቶች እርስ በእርሳቸው ተከራካሪ ወገን የሆኑባቸው የፍታሐብሔር ክርክሮች እርስ በእርሳቸው ተከራካሪ ወገን የሆኑባቸው የፍትሐብሔር ክርክሮች በድርድር እንዲያልቁ ድጋፍ ያደርጋል፤ • በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍትሐብሔር ክስ ለመመሥረት አቅም የሌለባቸው ዜጎች በተለይም ሴቶችንና ሕፃናትን ይከራከራል፤ • በወንጀል ጉዳዮች የዓለም ዐቀፍ ትብብርን በሚመለከት የሚፈፀሙ ሥራዎችን ያስተባበራል፤ • የሕግ ጉዳዮችን በሚመለከት የፌደራል መንግስት ዋና አማካሪና ሆኖ ይሰራል፤ • የሕግ ማሻሻያ ጥናቶችን እንዲሁም የኮዲፊኬሽንና የፌደራል ሕጎችን የማጠቃለል ሥራ ያካሄዳል፤ የክልሎችን ሕጎች ያሰባስባል፤ እንደ አስፈላጊነቱም እንዲጠቃለል ያደርጋል፤ • በፌደራል መንግስት አካላትና በክልሎች ጥያቄ ሲቀርብለት የሕግ ረቂቆችን በማዘጋጀት ይረዳል፤ • የወንጀል መነሻዎችን ያጠናል ፤ ወንጀል የሚቀንስበትን ስልት ይቀንሳል ፤ በዎንጀል ፤ በወንጀል መከላከል ረገድ የሚመለከታቸውን መንግስታዊ አካላትና ማህበረሰቡን ያስተባበራል፤ • የህዝቡን እንዲሁም የፌደራል መንግስትን መብትና ጥቅም ለማስከበር በማናቸውም የፍትሐብሔር ጉዳዮች ለፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶችና የልማት ድርጅቶችን በመወከል ሥልጣኑ በሚፈቀድለት ፍርድ ቤት ወይም በማነኛውም የክርክር የደረጃ ጣልቃ በመግባት ይከራከራል፤ • በፌደራል ፍርድ ቤቶች መከራከር ለሚችሉ ጠበቆች ፈቃድ ይሰጣል፤ ይቆጣጠራል፤ • የወንጀል ድርጊት ጠቋሚዎችና ምስክሮች በህግ መሰረት ጥበቃ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ • ሰብዓዊ መብት አጠባበቅ አንፃር የህዝቡን ንቃት ህግ ለማዳበር በተለያዩ ዘዴዎች የህግ ትምህርት ይሰጣል፤ የህግ ትምህርትና ስልጠናን በሚመለከት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የተባበራል፡፡ • በፍርድ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኙ የፌደራል ታራሚዎች የሚያቀርቡትን ይቅርታ ጥያቄ ተቀብሎ ያስተናግዳል፤ • ለፌደራል የህግ ታራሚ ተሰጥቶ የነበረው ይቅርታ እንዲሰረዝ ጥያቄ ሲቀርብ ተቀብሎ ያስተናግዳል፤ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች 

 ራዕይ

         በህብረተሰቡ ተሳትፎ የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የህዝብና የመንግስት አመኔታ የተቸረው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተቋም በ2017 ዓ.ም እውን ሆኖ ማየት፡፡

 ተልዕኮ

በሕግ ጉዳዮች የፌዴራል መንግስት ዋና አማካሪ እና ተወካይ በመሆን፤ የሕግ ማሻሻያ ጥናቶችን በማድረግ፣ በማርቀቅና በማስረፅ፣ የወንጀል ሕግን በማስከበር፣ ለወንጀል ጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥበቃ በማድረግ፣ የፌዴራል መንግስቱ ሕጎች ተግባራዊ መደረጋቸውን እና አተገባበራቸውም ወጥነት ያለው መሆኑን በማረጋገጥ፤በህግ ጉዳዮች የዓለም አቀፍ ትብብር ጉዳዮችን በማዕከላዊ ባለስልጣንነት በማከናወን፣ብሔራዊ የሰብአዊ መብት ድርጊት መርሀ ግብር ተግባራዊነቱን መከታተል ፣ልዩ ትኩረት ለሚሹና አቅም ለሌላቸው ዜጎች ተገቢው የህግ ድጋፍ በመስጠት፣የፌዴራል መንግስቱን እና የሕዝብን የፍትሐብሔር ጥቅም በማስከበር፣ ለጠበቆች ፈቃድ በመስጠትና በመቆጣጠር፤ የሕብረተሰቡንና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማሳደግ ፣ሕገ መንግስቱን እና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በማክበርና በማስከበር የህግ የበላይነት ማረጋገጥ፡፡

እሴቶች

¨  በሕግ የበላይነት የፀና እምነት

¨  የህዝብና የመንግሥትን ጥቅም ማስቀደም

¨  አሳታፊነት

¨  ግልፅነትና ተጠያቂነት

¨  ብልሹ አሠራርን መፀየፍ

¨  ለለውጥ ዝግጁነት

¨  በቡድን የመስራት ባህል

¨  የአገልጋይነት ስሜት

¨  ፍትሀዊነት

¨  ቅልጥፍናና ውጤታማነት

¨  በቅንጅት መሥራት

ሥልጣንና ተግባራት

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፦

፩/ የወንጀል ፍትህ ፖሊሲ የሚመለከታቸውን አካላት  በማስተባበር ያዘጋጃል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊነቱን ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤

፪/ በሕግ ጉዳዮች የፌዴራል መንግስት ዋና አማካሪ እና ተወካይ ሆኖ ይሰራል፤

፫/ የወንጀል ጉዳይን በተመለከተ፦

)  በሌሎች ህጎች ለፖሊስ የተሰጠው ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ በፌዴራል ፍርድ ቤት ስልጣን ስር የሚወድቅ የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር ያደርጋል፣  የተጀመረ የወንጀል ምርመራ ላይ የክትትል ሪፖርት እንዲቀርብ እንዲሁም ምርመራው በአግባቡ ተከናውኖ እንዲጠናቀቅ፣ በሕዝብ ጥቅም መነሻ ወይም በወንጀል የማያስጠይቅ ሁኔታ መኖሩ በግልፅ ሲታወቅ የወንጀል ምርመራ እንዲቋረጥ ወይም የተቋረጠው የወንጀል ምርመራ እንዲቀጥል ያደርጋል፣ ምርመራው በሕግ መሰረት መከናወኑን ያረጋግጣል፣ አስፈላጊውን ትእዛዝ ይሰጣል፤

፰ሺ፱፻፸

) በፖሊስ የተጀመረ የወንጀል ምርመራ እንዲያውቀው መደረግ አለበት፣ የምርመራ አካሄዱን በተመለከተ አስፈላጊውን ክትትል ያደርጋል፣ በምርመራ መዝገብ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ ከፖሊስ ድጋፍ ሊጠይቅ ይችላል፣ እንዲሁም በወንጀል  መዝገብ ላይ የተሰጠ የዓቃቤ ሕግና የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን ለሚመለ ከተው ፖሊስ ያሳውቃል፣ የወንጀል ምርመራ መዝገቦችን አስመልክቶ በየደረጃው ባሉ ዓቃቤያን ሕግ በተሰጡ ውሳኔዎች ላይ በፖሊስ የሚቀርቡ ይግባኞችን ተቀብሎ ውሳኔ ይሰጣል፤

) የተጠናቀቁ የምርመራ መዝገቦችን ከሕግና ከማስረጃ አንፃር መርምሮ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ መሰረት የተቀመጡ መመዘኛዎች ሲሟሉ የአያስከስስም ወይም የተዘግቷል ውሳኔ ይሰጣል፤

) የጥፋተኝነት ድርድር ይወስናል፣ ድርድር ያደርጋል፣ አማራጭ የመፍትሄ እርምጃ እንዲወሰድ ይወስናል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤

) የፌዴራል መንግስትን በመወከል የወንጀል ጉዳዩች ክስ ይመሰርታል፣ ይከራከራል፣ ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ክስ ያነሳል፣ የተነሳ ክስ እንዲቀጥል ያደርጋል:: ሆኖም ጉዳዩ ሀገራዊ ይዘት የሚኖረው ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩን በማማከር ክስ ስለሚያነሳበት አግባብ መመሪያ ያወጣል፤

) ፍርድ ቤቶች በወንጀል ጉዳይ የሚሰጡዋቸው ውሳኔዎችና ትእዛዞች መፈፀምና መከበራቸውን ይከታተላል፣ ሳይፈፀሙ ከቀሩ ወይም አፈፃፀማ ቸው ሕግን ያልተከተለ ከሆነ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለሰጠው ፍርድ ቤት በማመልከት የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ያደርጋል፤

፰ሺ፱፻፸፩

)  በፍርድ ቤት የሚወሰኑ የወንጀል ቅጣቶች በአግባቡ እንዲፈፀሙ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥርዓቶችን ያደራጃል ወይም መደራጀታቸውን ያረጋግጣል፤

)  የሞት ቅጣት ውሳኔዎችን ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ያቀርባል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡

፬/  የፍትሐ ብሔር ጉዳዮችን በተመለከተ፦

)  በፌዴራል የመንግስት መሥሪያ ቤቶች  የሕዝብ እና የፌዴራል መንግስት መብትና ጥቅም ወኪል ሆኖ ይከራከራል፣ ያስከብራል፣ እንዲከበሩ ያደርጋል፣ የሚከበሩበትን ሂደት ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤

)  በግዙፍ የመንግስት ፕሮጀክቶች የውል ዝግጅት እና ድርድር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያደርጋል፣ የሕዝብና የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ጥቅም ይጎዳል ብሎ ሲያምን በሌሎች ጉዳዮች ውል ዝግጅትና ድርድር ያደርጋል ወይም የሚመለከታቸውን አካላት ያማክራል፤

) የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤትን በመወከል የፍትሐ ብሔር ክስ ይመሰርታል፤ በከሰሱበት ወይም በተከሰሱበት የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ላይ ክርክር ያደርጋል፤ በተጀመረ ክርክር ተቋማትን ተክቶ በተናጠል ወይም በጋራ ይከራከራል፣ ወይም በክርክር አመራር ላይ ለመሥሪያ ቤቶች አቅጣጫ ይሰጣል፣ በሕግ መሠረት ፍርድን ያስፈፅማል፤

) የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች እርስ በርሳቸው ያልተግባቡባቸው የፍታሐ ብሔር ጉዳዩች በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጭ ባለ አማራጭ የክርክር መፍቻ መንገድ እንዲወሰን ውሳኔ ይሰጣል፣ በውሳኔው መሰረት መፈፀሙን ያረጋግጣል፤

  ፰ሺ፱፻፸፪

) በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍትሐብሔር ክስ ለመመሥረት የገንዘብ አቅም የሌላቸውን ዜጎች በተለይም ሴቶችን፣ ሕፃናትን፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን ወክሎ ይከራከራል፤

)  የገንዘብ አቅም የሌላቸው የወንጀል ተጎጂ የሆኑ ተበዳዩች እንዲካሱ መልሰው እንዲቋቋሙ እንዲሁም ከጉዳቱ የተያያዙ የፍትሐ ብሔር ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እነሱን በመወከል የፍትሐብሔር ክስ ያቀርባል ወይም ይደራደራል፤

)  የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በዓለምአቀፍ የዳኝነትና ከፊል ዳኝነት አካላት በሚከስበት ወይም በሚከሰስበት ጉዳይ መንግስትን በመወከል እና ከሚመለከ ታቸው አካላት ጋር በመመካከር ክርክር ያደርጋል፤ ድርድር ያካሂዳል፤ ውሳኔውንም ያስፈፅማል፤

፭/ የሕግ ማርቀቅ ሥራን በተመለከተ፦

)  በፌዴራል መንግሥት የሚወጡ ሕጎች  የሕግ ረቂቅ ዝግጅት ይሰራል፤ የመንግስት አካላት የሚያዘጋጁት ረቂቅ ሕግ ከሕገ መንግስቱና ከፌዴራል ሕጎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ያረጋግጣል፣ ለሚመለከታቸው ክፍሎችም አስተያየት ያቀርባል፤ በክልሎች ጥያቄ ሲቀርብለት የሕግ ረቂቆችን በማዘጋጀት ይረዳል፤

)  የሕግ ማሻሻያ ጥናቶችን እንዲሁም የኮዲፊኬሽንና የፌዴራል ሕጐችን የማሰባሰብና ማጠቃለል ሥራ ይሰራል፤ የክልል ሕጎችን ያሰባስባል፣ እንደአስፈላጊነቱም እንዲጠቃለሉ ያደርጋል፤

፰ሺ፱፻፸፫

) ኢትዮጵያ የምትፈርመው ወይም የምትቀበለው ዓለም አቀፍ ስምምነት ሕገ መንግስቱን እና የአገሪቱን ሌሎች ሕግጋት ያገናዘበና ከብሔራዊ ጥቅም አንፃር ተቀባይነት ያለው መሆኑን ያረጋግጣል፤

 ፮/ የፌዴራል መንግስቱ ሕጐች ተግባራዊ መደረጋቸውን እና አተገባበራቸውም ወጥነትያለው መሆኑን ያረጋግጣል፤ እንዲሁም አስፈፃሚ የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ሥራቸውን በሕግ መሰረት ማከናወናቸውን ያረጋግጣል፤

፯/ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ለፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት፣ ሹመኞች፣ ተመራጮች፣ ሰራተኞች እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ተሳታፊዎች እንደየአስፈ ላጊነቱ የሕግ ሥልጠና ይሰጣል ወይም እንዲሰጥ ያደርጋል፤

፰/ ሰብአዊ መብትን በተመለከተ፦

)  ነፃ የሕግ ድጋፍን አሰጣጥ ስትራቴጂዎችን  ይቀርፃል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ በመስኩ የሚሰማሩ አካላትን ያስተባብራል፤

)  ብሔራዊ የሰብአዊ መብት የድርጊት መርሀ ግብርን ከሚመለከታው አካላት ጋር በመሆን ያዘጋጃል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚመለከታቸውን አካላት ያስተባብራል፣ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ያቀርባል፤

) በፖሊስ ጣቢያና በማረሚያ ቤት ቁጥጥር ሥር ያሉ ሰዎችን ይጎበኛል፣ አያያዛቸው እና ቆይታቸው በሕግ መሰረት መፈጸሙን ያረጋግጣል፣ ሕገ ወጥ ተግባር እንዲታረም እንዲሁም ሕግን ተላልፈዋል በተባሉ ሰዎች ላይ በሕግ መሰረት እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤

፰ሺ፱፻፸፬

) የሰብአዊ መብት ትምህርት እና የንቃተ ሕግ ለማዳበር በተለያዩ ዘዴዎች ትምህርት ይሰጣል፤ በዘርፉ የተሰማሩ የሚመለከታቸውን አካላት ያስተባብራል፤

) ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸውን ወይም የተቀበለቻ ቸውን ዓለም አቀፍና አህጉራዊ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ ለሚነሱ ጉዳዮች እንደ አግባብነታቸው ከሚመለ ከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ምላሽ ይሰጣል፤ የስምምነቶቹን ብሔራዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጃል፤

፱/ ስለ ሕግ ጥናትና ስልጠና፦

 ሀ) አሰራሩን ውጤታማ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ጥናትና ምርምር ያደርጋል፤

) የወንጀል ፍትሕ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ ማደራጀት፣ መተንተንና ማሰራጨት የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፣ ያስፈፅማል፤

) ዓቃቤያነ ሕግ ስለ ስራቸው ያላቸውን አመለካከት፣ እውቀትና ክህሎት በተከታታይ እና በየደረጃው ለማሳደግ ሥልጠና ይሰጣል ወይም ስልጠና እና ትምህርት እንዲሰጣቸው ያደርጋል፤

፲/ የዓቃቤ ሕግ የውሳኔ አሰጣጥ እና የፍቅደ ሥልጣን  አጠቃቀም ወጥነትን ለማረጋገጥ በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የፀደቀ መመሪያ ተግባራዊ መደረጉን ያረጋግጣል፤

፲፩/       በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ደረጃ የጥብቅና አገልግሎት ለሚሰጡ ጠበቆች በሕግ መሠረት ፈቃድ ይሳጣል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤ ጠበቆችንና የጥብቅና አገልግሎትን ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል፤

፲፪/ በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር ፮፻፶፪/፪ሺ፩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስልጣንና ተግባር ስር የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ በወንጀልና ፍትሐብሔር ጉዳዩች ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ያደርጋል፤

፰ሺ፱፻፸፭

፲፫/ በዓቃቤያነ ሕግ የሚሰጡ ውሳኔዎች በሕግ መሰረት መከናወናቸውን የሚያረጋግጥ የኢንስፔክሽን ክፍል ያደራጃል፣ ጉድለቶችን በጥናት አስደግፎ ይለያል፤ በግኝቱ መሠረትም እንዲታረሙ ያደርጋል፣ አስፈላጊ ሲሆን እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፣ መልካም ተሞክሮዎችን ያስፋፋል፤

፲፬/ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር ፱፻፲፮/፪ሺ፰ የተመለከተውን የሚኒስትሮች የወል ሥልጣንና ተግባር  ሥራ ላይ ያውላል፤

፲፭/       የንብረት ባለቤትና የይዞታ ባለመብት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከሳል፣ ይከሰሳል፤

፲፮/ በሕግ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባራት ወይም ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

"ለሕግ፣ ለፍትህ፣ ለርትዕ !"