Search

 የህግ ማርቀቅና ማስረፅ ዳይሬክቶሬት

በፌዴራል መንግሥት የሚወጡ ሕጎች የሕግ ረቂቅ ዝግጅት ማድረግ፣ የመንግስት አካላት የሚያዘጋጁት ረቂቅ ሕግ ከሕገ መንግስቱና ከፌዴራል ሕጎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ማረጋገጥ፣ በሚዘጋጁ ረቂቅ ሕጎች ላይ ለሚመለከታቸው ክፍሎች አስተያየት መስጠት፣ በክልሎች ጥያቄ ሲቀርብለት የሕግ ረቂቆችን በማዘጋጀት እገዛ ማድረግ፣ የሕግ ማሻሻያ ጥናቶችን እንዲሁም የኮዲፊኬሽንና የፌዴራል ሕጐችን የማሰባሰብና ማጠቃለል፣ የክልል ሕጎችን የማሰባሰብና  አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ማጠቃለል ፣ ጥናትና ምርምር ማድረግ፣ የወንጀል ፍትሕ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ ማደራጀት፣መተንተንና ማሰራጨት የሚያስችል ስርአት መዘርጋት፣ የዐቃቢያነ ህግን  የአመለካከትና ክህሎት የሚያሳድጉ ተከታታይነት ያላቸውን ስልጠና ትምህርት እንዲሰጣቸው ማድረግ፣ እንዲሁም የሰባዊ መብት ትምህርትና የህብረተሰቡን ንቃተ ህግ የሚያሳድጉ ትምህርቶችን መስጠትና ከዚህ ጋር ተያያዝነት ያለውን ስራ ከሚሰሩ አካላት ጋር የማስተባበር ተግባረትን ተልእኮ ወስዶ የሚንቀሳቀስ ዳይሬክቶሬት ነው፡፡