Search

የኢኮኖሚ ወንጀል ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት

አደረጃጀት

ዚህ ዳይሬክቶሬት አራት ማስተባበሪያዎች የተደራጁ ሲሆን እነዚህም፡-

የታክስና የጉምሩክ ወንጀሎች ማስተባበሪያ፣

ከፀረ -ንግድ ዉድድር ጋር የተያያዙ ወንጀል ጉዳዮችማስተባበሪያ፣ እና

ልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ወንጀሎች ማስተባበሪያ

በወንጀል የተገኘ ንብረት ማስከበር፣ ማስወረስ እና ማስመለስ ማስተባበሪያ ናቸው፡፡


ዳይሬክቶሬቱ ስር ክትትል የሚደረግባቸው ወንጀሎች ምንነት /ባሕርይ/


በዚህ የሥራ ክፍል ስር የሚታዩ የወንጀል ጉዳዮች በዋናነት ኢኮኖሚያዊ ይዘት ያላቸዉ ሆነዉ በሀገር፣ በመንግስት፣ እንዲሁም በግለሰቦች ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀሎች ናቸዉ፡፡

እነዚህ የወንጀል ዓይነቶችም፡-


1ኛ.የታክስ እና የጉምሩክ ጋር የተያያዙ እና በሀገር እና በመንግስት ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ጉዳት የሚደርሱ ናቸዉ፡፡


2ኛ. የንግድ ዉድድር እና የሸማቾች መብት ጋር የተገናኙ ድርጊቶች ሆነዉ በሀገሪቱ ዉስጥ በሚደረጉ የንግድ እንቅስቃሴ ዉስጥ ያልተገቡና ህገ-ወጥ ድርጊት በመፈፀም ትክክለኛዉንና ህጋዊዉን አካሄድ በማዛባት የህጋዊዉን ነጋዴ፣ የሸማቹን መብት፣ እንዲሁም የመንግስትና የህዝብን ኢኮኖሚያዊ መብቶች የሚጎዱ ናቸዉ፡፡


3ኛ. የንግድ ምዝገባና ፍቃድ ጋር በተያያዘ የሚፈፅሙ ወንጀሎች የንግድ ምዝገባ አፈጻጸምና የንግድ ሥራ ፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት የነፃ ገበያ ኢኮኖሚን ለማራመድና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማስገኘት በሚያስችል መልኩ እዳይካሄዱ የሚያድርጉ እና በህጋዊዉ የንግድ ማህበረሰብ ብሎም በሀገር ላይ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት የሚያስከትሉ ወንጀሎች ናቸዉ፡፡4ኛ. የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የወጣውን አዋጅ በመተላለፍ የሚፈጸም ወንጀል (አዋጅ ቁጥር 721/2004) ይሁን እንጂ የመንግስት ሰራተኞች በስራቸው ምክንያት ለሚፈጽሙት ያልተገባ ድርጊት ተጠያቂ የሚሂኑበት የወንጀል ድርጊትን አይመለከትም፤


 

5ኛ. በወንጀል ህጋችን እና በተለያዩ አዋጆች ዉስጥ የተጠቀሱ በግለሰብ፣ በመንግስት እና በሀገር ንብረት፣ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ላይ የሚፈፀሙ እና ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀሎች ናቸዉ፡፡ከላይ የተጠቀሱትን በባህሪያቸዉ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት የሚያደርሱ የወንጀል ዓይነቶችን ይህ የስራ ክፍል የሚይዛቸዉ እና ክትትል የሚያደርግባቸዉ ብሎም እስከታችኛዉ መዋቅር ድረስ ወርደዉ ሲሰሩም የሚከታተላቸዉ ይሆናሉ፡፡

 

የኢኮኖሚ ወንጀሎች በማዕከል እና በክ/ከተማ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤቶች እንዲታዩ ለመወሰን በዋና መመዘኛነት የተቀመጡ የመለያ መስፈርቶች፡-


የግብር ከፋዮች ደረጃ እና ባህሪ፣


ወንጀሎቹ የሚያስከትሉት ቅጣት፣


የወንጀሎቹ ባህሪ እና ውስብስብነት፣


የኃላፊዎች የቅርብ ክትትል አስፈላጊነት፣


የወንጀሎቹ ስፋት እና የስርጭት ወሰን፣


የወንጀሎቹ ተሳታፊዎች ባህሪ እና የወንጀለኞቹ ብዛታቸው፣


በዳይሬክቶሬቱ እና በክ/ከተማ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤት የሚታዩ የጉምሩክ ወንጀሎች


በዳይሬክቶሬቱ የሚታዩ የጉምሩክ ጉዳዮች፣


ሰነዶችን፣ መለያዎች ወደ ሀሰተኛ መለወጥ እና አስመስሎ መሥራት፣


በተደራጀ መንገድ የሚፈፀሙ የኮንትሮባንድ ወንጀል፣


የንግድ ማጭበርበር /ውስብስብ/ወንጀል፣


በተደራጀ መንገድ የሚፈፀሙ እሽግ መፍታት እና ምልክቶችን ማንሳት ወንጀሎች፣


በድርጅቶች የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣


በክ/ከተማ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ጽ/ቤት ደረጃ የሚታዩ የጉምሩክ ጉዳዮች፣


የጉምሩክ ቁጥጥርን ማሰናከል ወንጀል፣


መደበኛ የኮንትሮባንድ ወንጀሎች፣


የአጓጓዥ ግዴታዎችን በመጣስ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣


ከኤሌክትሮኒክስ መረጃዎች ልውውጥ ጋር የተያያዙ ወንጀሎች፣


መደበኛ እሽግ መፍታት እና ምልክቶች ማንሳት ወንጀል፣


በዳይሬክቶሬቱ እና በክ/ከተማ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት የሚታዩ የታክስ ወንጀሎች


በዳይሬክቶሬቱ የሚታዩ የታክስ ወንጀሎች፣


ሀሰተኛ ወይም አሳሳች መግለጫና የተጭበረበሩ ሰነዶች ወንጀሎች፣


ከህገ-ወጥ ደረሰኞች ጋር የተያያዙ ወንጀሎች፣


ህገ-ወጥ ተመላሽ ወይም ማካካሻ ጋር የተያያዙ ወንጀሎች፣


ታክስ ስወራ ወይም ማጭበርበር፣


የታክስ ወንጀልን መርዳት ወይም ማበረታታት፣


በባለስልጣኑ ያልተፈቀደ ማሽን መጠቀም፣


በባለስልጣኑ ያልተፈቀደ ሶፍትዌር ለገበያ ማዋል፣


ፈቃድ ሳይኖር ማሽን ወይም ሶፍትዌር ማቅረብ፣


በድርጅቶች አማካኝነት የሚፈፀሙ የታክስ ወንጀሎች፣


በክ/ከተማ የፌዴራል ጠቅላይዐቃቤሕግጽ/ቤት ደረጃየሚታዩ የታክስ ወንጀሎች


ከግብር ከፋይ የመለያ ቁጥር ጋር የተያያዙ ወንጀሎች፣


ያለደረሰኝ ግብይት፣


በአንድ ግብይት የተለያዩ ዋጋዎችን መመዝገብ፣


ግብይት ሳይፈፀም ደረሰኝ መስጠት፣


ያለባለስልጣኑ ፈቃድ ደረሰኝ ማሳተም፣


ለተጨማሪ እሴት ታክስ ሳይመዘገብ ደረሰኝ መስጠት፣


ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ዴቢት ወይም ክሬዲት ወንጀሎች፣


ከቴምብር ቀረጥ ጋር የተያያዙ ወንጀሎች፣


ታክስ ለማስከፈል ከሚወሰዱ እርምጃዎች ጋር የተያያዙ ወንጀሎች፣


የታክስ ህጎች አፈጻፀም እና አስተዳደሩን ማሰናከል፣


ስልጣን ሳይኖር ታክስ መሰብሰብ፣


የታክስ ወንጀል እንዲፈፀም መርዳት ወይም ማበረታታት፣


ከታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ጋር የተያያዙ ወንጀሎች፣


በታክስ ወኪሎች የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣


ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ጋር የተያያዙ ወንጀሎች፣ 


በዳይሬክቶሬቱ እና በክ/ከተማ ጠቅላይ ዐ/ህግ ጽ/ቤት ከፀረ-ንግድ ውድድር እና ከሸማቾች ጋር በተያያዘ የሚታዩ ወንጀሎች

በዳይሬክቶሬቱየሚታዩጉዳዮች፣


በቀድሞ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 686/2002 እንዲሁም በንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008  መሠረት የንግድ ሚ/ር እና ሌሎች ሚ/ር መ/ቤቶች እንዲሁም የፌዴራል ተቋማት የንግድ ፈቃድ በሚሰጧቸው የንግድ ድርጅቶች የሚፈፀሙ የፀረ-ውድድር ተግባራት እና የሸማች ጥበቃን የሚመለከቱ ወንጀሎች /የግል ድርጅቶች፣ ኃላፊነት የተወሰነ የግል ማህበራት እና አክሲዮን ማህበራት/፣


ከፒራሚድ ሽያጭ ስልት /ኔትዎርክ ማርኬቲኒግ/ ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣


አስገዳጅ የጥራት ደረጃ ምልክትን መጠቀም ሲኖርባቸው ያለመጠቀም፣ የጥራት ደረጃቸው የወረደ የንግድ ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን የማምረት ወይም የማስመጣት ወይም የማከፋፈል ድርጊቶች እና በሚዲያ ሀሰተኛ ወም የተሳሳተ ማስታወቂያ የማስተላለፍ ድርጊት ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣


ከንግድ ምልክት እና ሌሎች የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ጋር በተያያዙ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣


በአዋጅ 980/2008 የተቀመጡ ድንጋጌዎች ጋር በተያያዙ የሚፈፀሙ ወንጀሎች - በፌዴራል ደረጃ የተመዘገቡና ፈቃድ ያወጡ ነጋዴዎች ሲሆኑ፣


በንግድ ውድድሮች የሸማቾች ጠበቃ ባለስልጣን በዳኝነት ችሎት አስተዳደራዊ እርምጃ እና ቅጣት ተጥሎባቸው የችሎቱን ውሣኔ የማያከብሩ ወይም ከፀረ-ውድድር ተግባር የማይቆጠቡ ከሆነ ጉዳያቸው በወንጀል ድርጊት የሚጠየቁ ሲሆን ጉዳያቸው በማዕከል ይታያል፡፡


በክ/ከተማ ጠቅላይ ዐ/ሕግ ጽ/ቤት ደረጃ የሚታዩ ጉዳዮች፣


ከላይ በማዕከል እንደሚታዩ ከተዘረዘሩት ውጭ የሚፈፀሙ የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃን ሚመለከቱ ወንጀሎች በተለይም በአ/አ ከተማ መስተዳደር ውስጥ የተፈፀሙ እንደሆነ፣


በአ/አ ንግድ ቢሮ ወይም በየክልል ከተማና ወረዳ ካሉ የንግድ ጽ/ቤቶች የንግድ ፈቃድ ባወጡ የንግድ ድርጅቶች ወይም ግለሰብ ነጋዴዎች የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣


ነጋዴ ባልሆኑ ወይም የንግድ ፈቃድ በሌላቸው ግለሰቦች የሚፈፀሙ የሸማቾች ጥበቃን በሚመለከት ወይም ከፀረ-ውድድር ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣


በድሬዳዋ ከተማ የሚፈፀሙ የፀረ-ውድድር እና ከሸማቾች ጥበቃ ጋር የተያያዙ ወንጀሎች በከተማው በሚቋቋመው የፌዴራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ የሚታይ የሆናል፡፡


በዳይሬክቶሬቱ እና በክ/ከተማየፌዴራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ ጽ/ቤት የሚታዩ ልዩ ልዩ

የኢኮኖሚ ወንጀሎች


በዳይሬክቶሬቱ  የሚታዩጉዳዮች፡-


ርዕስ ሶስት ስር ከአንቀጽ 343- 354 ድረስ የተገለፁ በመንግስት የኢኮኖሚ እና የገንዘብ ጥቅሞች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣

ርዕስ አምስት ስር ከአንቀጽ 356-362 ድረስ የተገለፁ የታወቁ የገንዘቦች፣ የግዴታ ወይም የዋስትና ሰነዶች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣


የአራጣ ወንጀሎች፣


የገንዘብ ዝውውር ወንጀል /ሀሰተኛ ገንዘብ ህትመትና የውጪ ሀገር ገንዘብ ዝውውር ወንጀል/፣


ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ወንጀሎች ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ በሕገወጥመንገድየተገኘንገንዘብሕጋዊአስመስሎማቅረብወንጀል፡፡


በክ/ከተማ የፌዴራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ  ምድብ ጽ/ቤቶች ደረጃ  የሚታዩ ልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች


ቀደም ሲል በክፍለ ከተማ በተደራጁት ጽ/ቤቶች ደረጃ ይታዩ የነበሩ ልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ወንጀሎች በቀድሞው አግባብ አሁንም በክፍለ ከተማ ስልጣን ስር የሚታዩ ይሆናሉ፡፡ በዚህም መሠረት፡-


የወንጀል ቅጣታቸው ከ15 ዓመት ጽኑ እስራት በታች የሆኑ ልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ወንጀሎችን፣

በምርመራ ሂደታቸው ውስብስብ ያልሆኑ ልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ወንጀሎችን፣


በወቅታዊነታቸው ምክንያት በአንድ ማዕከል መያዛቸው አስፈላጊ የማይሆኑ፣


በግልጽ ለዳይሬክቶሬቱ ያልተሰጡ ልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች፣


በጽ/ቤቶች ስልጣን ስር ከሚወድቁ ልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ወንጀሎች ጋር በተያያዘ በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብ ወንጀሎች በምድብ ጽ/ቤቶች የሚታዩ ይሆናሉ፡፡


ማስታወሻ

ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ከሁለት እና ከዚያ በላይ   ክልሎች ወይም ክ/ከተሞች የተፈፀሙ የታክስ ወይም የጉምሩክ ወንጀሎች በማዕከል የሚታዩ ይሆናል፤ እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ በዳይሬክቶሬቱ በልዩ ሁኔታ የሚሳቡ ወንጀሎች በማዕከል ይታያሉ፡፡


በኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬቱ ስር ተደራጁ ማስተባበሪያዎች  የሚከታተሏቸው ጉዳዮች ዝርዝር

በስራ ሂደቱ በተደራጁ ማስተባበሪያዎች ስር ክትትል የሚደረግባቸው ጉዳዮች፡-

ታክስና የጉምሩክ ወንጀሎች ማስተባበሪያ፣

የጉምሩክ እና ታክስ ህጎችን (የገቢ ግብር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ኤክሳይስ ታክስ፣ ተርን ኦቨር ታክስ….

የገቢ ግብር አዋጅ 285/1994 እና ማሻሻያ አዋጆቱ ላይ የተጠቀሱ ወንጀሎች..

የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ 286/1994 ማሻሻያ አዋጆቱ ላይ የተጠቀሱ ወንጀሎች

ተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ 308/1995 ማሻሻያ አዋጆቱ ላይ የተጠቀሱ ወንጀሎች..

ኤክሳይስ ታክስ አዋጅ 307/1995 ማሻሻያ አዋጆቱ ላይ የተጠቀሱ ወንጀሎች..

የማዕድን ልማት ገቢ ግብር አዋጅ 53/1985 ማሻሻያ አዋጆቱ ላይ የተጠቀሱ ወንጀሎች

ሌሎች የታክስ አይነቶች ላይ የተገለፁ ሌሎች ወንጀሎች..

የጉምሩክ አዋጅ 859/2006 በመተላለፍ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ፤ 

ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ወንጀሎች ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ በህገወጥመንገድየተገኘንገንዘብሕጋዊአስመስሎማቅረብወንጀል፡፡


ከፀረ-ንግድ ዉድድር ጋር የተያያዙ ወንጀል ጉዳዮች ማስተባበሪያ


የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 ላይ የተጠቀሱ ወንጀሎች፣

የፀረ ዉድድር የሆኑ የንግድ አሰራሮች ወንጀሎች፣

የሸማቾችን መብት የሚጥሱ ተግባራት ወንጀሎች፣

የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ሰለሚገኙ ጉድለቶች እና የተከለከሉ ተግባራትን መፈፀም ወንጀሎች፣

ስለ ንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ስርጭት (እንደ ማከማቸት ያሉ) ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣

የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ 686/2002 ላይ የተጠቀሱ ወንጀሎች፤

ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ወንጀሎች ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ በህገወጥመንገድየተገኘንገንዘብሕጋዊአስመስሎማቅረብወንጀል፡፡


ልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ወንጀሎች ማስተባበሪያ


በኢፌዴሪ ወንጀልሕግ፡-

ርዕስ ሶስት ስር ከአንቀፅ 343- 354 ድረስ የተገለፁ በመንስት የኢኮኖሚ እና የገንዘብ ጥቅሞች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣

ርዕስ አምስት ስር ከአንቀፅ 356-362 ድረስ የተገለፁ የታወቁ የገንዘቦች፣ የግዴታ ወይም የዋስትና ሰነዶች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣

የገንዘብ ዝውውር ወንጀል /ሀሰተኛ ገንዘብ ህትመትና የውጪ ሀገር ገንዘብ ዝውውር ወንጀል፣

የአራጣ ወንጀሎች

ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ወንጀሎች ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ በሕገወጥመንገድየተገኘንገንዘብሕጋዊአስመስሎማቅረብወንጀል፡፡

በወንጀል የተገኙ ንብረቶች ማስከበር፣ ማስወረስ እና ማስመለስ ማስተባበሪያ

ከላይ በተጠቀሱት ወንጀሎች ለወንጀሉ መፈተሚያ የዋሉ ንብረቶችን ወይም ከወንጀሉ ፍሬ ሆነው የተገኙ ንብሬችን በመከታተከል እና በመለየት በህጉ መሰረት እንዲከበር እንዲወረስ እና በወንጀሉ ምክንያት የጠፋ ሃብት ወይም የደረሰ ጉዳት ካለ እንዲካስ የማድረግ ሃላፊነትን የሚወጣ ቡድን ይሆናል፡፡  የኃላፊ ስም፡-  አቶ አንተነህ አያሌው


የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-2-73-31-65