Search

የዓለም አቀፍ ትብብር፣ የሰብዓዊ መብቶችና የፀረ-ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ዳይሬክቶሬት

 ይህ ዳይሬክቶሬት በዋናናነት በወንጀልና ፍታብሄር ጉዳዮች ዓለም አቀፍ ግንኑነትና ትብብር ማድረግ ፣አገራችን በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ሕጎችን እና መርሆዎች፣ የሁለትዮሽ ወይም ከብዙ አገሮች ጋር በመሆን የሚደረጉ ስምምነቶች ወይም የአገር ውስጥ የሕግ ማዕቀፎችን መነሻ በማድረግ በዓለም አቀፍ ፍ/ቤቶች የተመሰረቱ የወንጀል ክሶችን፣ ዓለም አቀፍ ባህሪ ባላቸው ወንጀሎች ላይ የሚደረጉ ምርመራዎችን፣ የወንጀል ምስክሮችን እና ሰለባዎችን አስመልክቶ የሚደረጉ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን  ማስተባበር፣ የፍ/ቤት ውሳኔዎችን ዕውቅና መስጠት እና ማስፈፀም፣ የወንጀል ክስን ወደ ሌላ አገር ማስተላለፍ፣ አሳልፎ መስጠት፣ የወንጀል ፍሬዎቸን እና ገንዘብን ማገድ እና መውረስ እና መሰል ዓለም አቀፍ ትብብርን የሚጠይቁ የፍትሕ ስራዎችን አስመልክቶ በአገር ውስጥ እና በአገር ውጭ የሚከናወኑ ተግባራትን የማስተባበር፣ ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸውን ወይም የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍና አህጉራዊ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ ለሚነሱ ጉዳዮች እንደ አግባብነታቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ምላሽ ይሰጣል፤ የስምምነቶቹን ብሔራዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጃል፣ የብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብር አፈጻፀም መከታተልና ሪፖርት ለሚመለከተው አካል አዘጋጅቶ ያቀርባል፣ የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ግብረ ሀይል በማቋቋም ሂደቱን የመከታተል ተልኮ ተሰጥቶት የሚንቀሳቀስ ክፍል ነው፡፡