Search

የፍትሐብሔር ፍትሕ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የፌዴራል መንግስቱ ወኪል ሆኖ መከራከር፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የግዙፍ የመንግስት ፕሮጄክቶችን የውል ዝግጅትና በተዘጋጁት ላይ መመርመርና ሀሳብ መስጠት፣ ድርድር ማድረግ፣  የፌዴራል የመንግስት መ/ቤቶች እርስ በርሳቸው ባልተግባቡባቸው የፍትሐብሔር ጉዳዮች ላይ በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጭ ባሉ አማራጭ የሙግት መፍቻ መንገዶች መፍትሄ እንዲያገኙ መወሰንና አፈፃፀሙን መከታተል፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መንግስት በዓለም አቀፍ የዳኝነትና ከፊል ዳኝነት አካላት በሚከስበት ወይም በሚከሰስበት ጉዳይ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን መንግስትን በመወከል መከራከር፣ መደራደር፣ ውሳኔዎችን ማስፈፀም እንዲሁም አቅም ለሌላቸው ሴቶችና ህፃናት ወክሎ የፍታብሄር ክርክር በማድረግ ጥቅማቸውን ማስከበር የሚመለከቱ ጉዳዮችን በዚህ ዳይሬክቶሬት ስር በሀላፊነት የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው፡፡