Search


ይቅርታና የምህረት ቦርድ ጽቤት


ይህ ጽ/ቤቱ በታራሚዎችና በፍርደኞች የሚቀርቡ የምህረትና የይቅርታ ጥያቄዎችን ተቀብሎ የሚያስተናግድ ሲሆን ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነቱም፡-


ከህግ ታራሚዎች በግል የሚቀርቡ የይቅርታ ጥያቄ በመመርመር ለይቅርታ ቦርድ ማቅረብ፣

በይቅርታ ቦርድና በማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ጥናት ይቅርታ ለሚገባቸው ይቅርታ ማስረጃ መርምሮ ለይቅርታ ቦርድ ማቅረብ፣

 

የቦርዱ አባላት ውሣኔ ሃሣብና ይቅርታ ይገባቸዋል የተባሉት ታራሚዎችን መግለጫ ለፕሬዘዳንት ጽ/ቤት መላክ፣

 

ይቅርታ ይገባቸዋል ተብሎ የምሥክር ወረቀት ከፕሬዘዳንት ጽ/ቤት ሲላክ ለማረሚያቤት መላክና ታራሚዎች መውጣታቸውን መከታተል፣

 

ይቅርታ ውድቅ የተደረገባቸውን ታራሚዎች እንዲያውቁት በቦርድ የተሰጠውን ምክንያትት በደብዳቤ ማሣወቅ፣

 

በተጨበረበረ ማስረጃዎች የወጡ ታራሚዎችን መረጃ መርምሮ ለቦርድ በማቅረብ ውሣኔ ማሰጠት፣

 

ፕሬዘዳንቱ ውሣኔውን ሲያፀድቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ይቅርታ እንዲገባ ማድረግ

 

ለማረሚያ ቤቶቹ አስተዳደር ክልል ማረሚያቤቶች አገልግሎት አሠጣጥና አፈፃፀም ተግዳሮትና መፍትሔ ዙሪያ ሥልጠና መስጠት፣

 

የሞት ፍርዶችን መረጃ አጠናቅሮ ለኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት ጽ/ቤት መላክ እንዲፈጸም ሲወሰን ከማረሚያ ቤት ጋር በመሆን አፈፃፀሙን መከታተል፣

 

ክልል ይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤቶችን በመጎብኘት በይቅርታ አሠጣጥና አፈፃፀም ላይ የተስተዋሉ ችግሮችን እንዲቀረፍ አብሮ መስራት፣

 

በይቅርታ አሠጣጥ ዙሪያ የሚቀርቡ አቤቱታዎች አይቶ ከሚመለከተው አካል ጋር መፍትታት፣

በዓመት አንድ ጊዜ ከክልልና የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ጋር በአሠራር የተገኙት ምርጥ ተሞክሮች ውስጥ ዙሪያ የልምድ ልውጥ በማድረግ የጋራ ግንዛቤ  በመያዝ የተሻለ ተሞክሮ ወስዶ ጥቅም ላይማዋል እና

 

ይቅርታ ተደርጎላቸው ወደ ህዝብ የተቀላቀሉ በይቅርታ ተጠቃሚዎች ህብረተሰቡ ጋር በሠላም ስለ መኖሩ ጥናት ማድረግ የጥናቱን ውጤት መተግባር፣


 የኃላፊ ስም፡-   አቶ ዘለቀ ዳለሎ


 የቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 011-5-53-17-05