Search

በወንጀል የተገኘ ንብረትን ከመለየት፣ ከማሳገድ፣ ከመውረስና ከማስተዳደር አንፃር ያለውን አስራር ለማጠናከር በማሰብ ከተለያዩ የፍትህ ተቋማት ለተወጣጡ አካላት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

Published: 286 days ago

በወንጀል የተገኘ ንብረትን ወይንም የወንጀል ፍሬ የሆነ ገንዘብን የመለየት፣ የማሳገድ ፣ የመውረስና የማስተዳደር አቅምን ለመገንባት ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለተወጣጡ ዐቃቤያነ ሕጎችና የፖሊስ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

 

ሥልጠናው በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማስረጽ ዳይሬክቶሬት አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡

 

በሥልጠናውም በወንወጀል ምርመራና ክስ ዝግጅት ዘርፍ የሚሰሩ 38 አቃቤያነ ሕጎችና 12 መርማሪ ፖሊሶች በአጠቃላይ 50 ስልጣኞች ተሳታፊ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ ጥናት ማርቅቅና ማስረጽ ደይሬክቶሬት ም/ዳይሬክተር የሆኑት አቶ እንዳልካቸው ወርቁ የስልጠናውን አስፈላጊነት በአብራሩበት ወቅት ወንጀለኞችን ተከታትሎ ከማስቀጣቱ ጎን ለጎን በወንጀል የተገኘውን ንብረት ወይንም የወንጀል ፍሬ የሆነውን ገንዘብ የመለየት፣ የማሳገድ ፣ የመውረስና የማስተዳደር አቅምን መገንባት ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

 

ም/ዳይሬክተሩ አያይዘውም በወንጀል ምርመራና ክስ ዝግጅት ዘርፍ የሚሰሩ ዐቃቤያነ ሕጎችንና የፖሊስ አባላትን ግንዛቤ በማሳደግ ወቅቱ የሚጠይቀውን የወንጀል መከላከልና የመቆጣጠር ስትራቴጂ የመዘርጋት ተግባር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል በማለትም ተናግረዋል ፡፡

 

በስልጠናውም ወንጀለኞችን በእስራት ከማስቀጣት ጎን ለጎን በወንጀሉ መፈፀም የሚገኘውን ጥቅም ተከታትሎ በማክሰምና የወንጀል ፍሬ የሆነውን ማንኛውም ገንዘብና ንብረት እንዲወረስ በማድረግ እንዲሁም በሕግ አግባብ በማሳገድና በማስተዳደር የወንጀለኞችን አቅም ማሳጣትና የህብረተሰቡን ከወንጀል የመጠበቅ መብት ማረጋገጥ ይገባል ተብሏል፡፡


###

455016216_338929.jpg