Search

ክቡር ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ብርሀኑ ጸጋዬ ከቻይናው ፍትህ ሚኒስቴር ሉዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡

Published: 265 days ago

ኢትዮጵያና ቻይና በፍትህ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በቻይና ፍትህ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር የተመራ የሉኡካን ቡድን ከክቡር ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ ከአቶ ብርሀኑ ጸጋዬ ጋር ውይይት አደረጉ ፡፡

 

በውይይት መድረኩ ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ቻይና በኢትዮጵያ በመሰረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ የምታደርገውን ድጋፍና ተሳትፎ አድንቀው ተቋማችን የሀገሪቱን የሕግ በላይነት ከማስጠበቅና የፍትህ ሪፎርሙን ከማዘመን ጋር ተያይዞ በተለይም በሙስና፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀሎች ጋር ተያይዞ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የፍትህ ሰርዓቱን የበለጠ ተደራሽ ለማደረግ በአቅም ግንባታ ዘርፍ የቻይና መንግስትን ድጋፍና ተሳትፎ ኢትዮጵያ መጠቀም እንደምትፈልግ ገልጸዋል፡፡

 

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የህግ የበላይነትን ከማስጠበቅ ጋር ተያይዞ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እያከናወነ ያለውን ተግባር የሚበረታታ ሆኖ ከአቅም ግንባታና ከቴክኒካል ድጋፍ ጋር ተያይዞ የቻይና መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ በቻይና የፍትህ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር የሆኑት Mr.Liu Zhenyu ገልጽዋል፡፡

 

በተጨማሪም ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ ተከትሎ በፍትህ ስርዓቱ ላይ የተጀመረውን ሪፎርምም የቻይና መንግስት ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ምክትል ሚኒስትሩ አክለው ገልጽዋል፡፡


በመጨረሻም የሀገራቱን የቆየ ዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነት ከማጣናከር ባሻገር በህግ የበላይነት ላይ በጋራ ለመስራት ተቋማቱ ተስማምተው፤ በቀጣይም በመንግስት ከተሰጣቸው ተግባርና ኃላፊነት ጋር ተያይዞ በፍትህ ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ በቀጣይ እንደሚፈራረሙ ተመላክቷል፡፡


###

66411584_2348804271880310_1437356452518821888_o.jpg  66300717_2348803885213682_2123266917283135488_o.jpg