Search

የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አመራሮች እና የሕግ ታራሚዎች በጋራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናወኑ

Published: 260 days ago

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች ከሕግ ታራሚዎች ጋረ በመሆን አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው በአዲሱ ማሪሚያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናውነዋል፡፡

 

ክቡር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ እንደተናገሩት የዛሬው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ዋና አላማ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተመናመነ የመጣውን የድን ሀብት መልሶ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ጠቀሜታ እንዲኖረው ለማድረግ እና የማረሚያ ቤት ታራሚዎች በሚታረሙበት ወቅት ሰራተኛውና ታራሚው እንደ ቤተሰብ ሆኖ ታራሚዎች የመታረምን፣ የመታነጽን አስተሳሰብ እንዲያዳብሩ እንዲሁም በዚህ ሂደት ተፀፅተው ነገ ከወንጅል ነፃ ሆነው በአገሪቱ እድገት የራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ እድል ለመስጠትና ለማስተማር ብሎም መልዕክት ለማስተላለፍ ሲሆን በአዲሱ ማረሚያ ቤት በሚተከለው ቸግኝ የራሳቸውን አስተዋጾ እንድያበረክቱ መሆኑን ጠቁመው በሀገር አቀፍ ደረጃ የተላለፈውን የአርንጓዴ ልማት ጥሪን ለመወጣት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

የማረሚያ ቤቶች የፋይናስና የሰው ኃይል ልማት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ኮሚሽነር ያረጋል አደመ በፖሊስ አባላት እና በታራሚዎች መካከል ቤተሰባዊ ግንኙነት በማጠናከር እና እርስ በእርስ በመግባባት ብሎም ተልዕኮን በመፈፀም ታራሚዎችን በሀገር ልማት ወስጥ ተሳታፈ በማድረግ አገራዊ ኃላፊነትን መወጣት መቻሉን ገልፀው በሺዋሮቢት እና በዝዋይ ማሪሚያ ቤቶችም ከ400 ሺ በላይ ችግኞችን ለመትከል በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

በማረሚያ ቤት በከፍተኛ ጥበቃ ስር የሚገኘው የሕግ ታራሚ ዲያቆን ዳንኤል ተሾመ በማረሚያ ቤቱ የዞን የሰላም ኮሚቴ ሰብሳቢ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ ባስተላለፉት መልዕክት መሰረት በሕግ ጥላ ስር የምንገኝ ታራሚዎች በአገር ደረጃ የ4 ቢሊዮን ችግኝ ተከለ ግብ ለማሳካት በመሳተፋቸው ደስታ የተሰማቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

በመጨረሻም ክቡር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ‹‹ደን ከሌለ አየር የለም፣ አየር ከሌለ ሰው የለም፣ ሰው ከሌለ አገር የለም›› በማለት ችግኝ መትከል ማለት ሰውም አገርም እንዲኖር ማድረግ መሆኑን ገልጸው የሕግ ታራሚዎች መልካም ዜጋ በመሆን ለአገራቸው ልማት አስተዋጾ እንዲያደርጉ እና በቀጣይ በመታረምና በመታነጽ ሂደት ወሰጥ ራሳቸውን የሚለውጡበት ሁኔታ ከሚቀጥለዉ ዓመት ጀምሮ መንግስት በትኩረት የሚሰራ መሆኑን በመግለፅ በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ለተገኙ የሕግ ታራሚዎችና አመራሮች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


###

66475466_2355215881239149_3540471056831610880_o.jpg  66478239_2355216864572384_5739845876931624960_o.jpg