Search

ተቋሙ የ2011 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ ላይ ውይይት ሊያደርግ ነው

Published: 178 days ago

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የ2011 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2012 ዕቅድ ትውውቅን አስመልክቶ ከሐምሌ 26 እስከ 29 ባለው ጊዜ በሶደሬ ሪዞርት ከተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ከተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ሊያደርግ መሆኑ ታውቋል፡፡

 

በውይይት መድረኩ በ2011 በጀት ዓመት በዕቅድ አፈጻጸሙ ላይ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን ከመገምገም ባሻገር ለቀጣዩ በጀት ዓመት አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተበሎ ይጠበቃል፡፡

 

በመድረኩ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ እንግዶችና የህዝብ ክንፍ አባላት የሚሳተፉ ሲሆን በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ዳይሬክቶሬቶችና ፈፃሚዎች ዕውቅና እንደሚያገኙም ታውቋል፡፡


###

52898317_2133343180093088_4237424999205437440_n.jpg