Search

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የ3ኛ ዙር የ100 ቀን እቅድ አፈፃፀሙን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ከመጡ አካላት ጋር ገመገመ

Published: 164 days ago

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የ3ተኛውን ዙር የ100 ቀናት እቅድ አፈፃፀሙን አስመልክቶ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ከመጡ አካላት ጋር በመሆን በዛሬዉ እለት ገምግሟል፡፡

 

የእቅዱን አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የፍትህ ስርአት ማሻሻያ እና እቅድ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ በረከት ማሞ ተቋሙ የ100 ቀናት እቅዱን ለመፈፀም ሲነሳ 3 መሰረታዊ ተግባራት ላይ ማለትም የህግ የበላይነትና ፍትህ ስርአት ግንባታ፣የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥን ከማሻሻልና የሰዉ ሀብትና አቅም ግንባታ ላይ መሰረት አድርጎ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን አቅርበዋል፡፡

 

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ታራሚዎች ታርመዉና ታንፀው እንዲወጡ ከማድረግ፣መመሪያዎችን ከማሻሻል፣የተሸሻሉና አንደ አዲስ የሚዘጋጁ ህጎችን የማርቀቅ ተግባራት፣የሰብአዊ መብት ጥሰትና ሙስና ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦችን ተጠያቂ ከማድረግ፣የተደራጁ ወንጀሎችን ተግባራት መርምሮ ስራን ማጠናቀቅ በተመለከተ በሁሉም ቦታ እየተሰራ እንደሆነ በሪፖርቱ የቀረበ ሲሆን እንዲሁም በህገ ወጥ የሰዎች ዝዉዉር፣የገንዘብና ህገወጥ የመሳሪያ ዝዉዉሮች ላይም ስራዎች ተሰርተዉ በርካታ መሳሪያዎችና ገንዘቦች እንደተወረሱ ተጠቁሟል፡፡

 

የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል ተግባር ስር የዘመናዊ የምርመራ ስራዎችን ለማከናወን የሚያግዙ መሳሪያዎችን ለማሟላት ስራዎች መሰራታቸዉን የገለፁት አቶ በረከት በከባድ ወንጀሎች የማጥራት ምጣኔ ማሳደግ ከመቻሉም በተጨማሪም ምስክርና ተከሳሽ ባለመቅረብ የሚቋረጡ መዝገቦችንም መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል፤ በፍትሀ ብሄር አስተዳደር በኦዲት ግኝቶች የተመዘበሩ የአገርና የህዝብ ሀብቶች ዉስጥ 39 ሚሊየን ብር በዚሁ የ100 እቅድ አፈፃፀም ማስመለስ መቻሉም በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡

 

በተጨማሪም በዚሁ የ3ተኛዉ ዙር የ100 ቀን እቅድ ላይ ሌሎች ተጨማሪ ተግባራት መከናወናቸዉን ያከሉት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ብርሀኑ ፀጋዬ በተለይም የህግ የበላይነትን ለማስከበር በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች የተከሰቱ የብሄር ተኮር ግጭቶችን በማጣራትና በበላይነት በመምራት በርካታ ስራዎች መሰራታቸዉን ተናግረዉ ህጎችን በማሻሻል እና አሰራርን በመቀየር ጭምር ሰፊ የባለ ድርሻ አካላት መድረክ ተፈጥሮ ስራዎች መሰራታቸዉን አክለዋል፡፡

 

ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ አያይዘዉም በቀጣይ 100 ቀናት የትኩረት አቅጣጫ ናቸዉ ያሏቸዉን ሀሳቦች ያነሱ ሲሆን ከነዚህ ዉስጥም የህግ የበላይነትን ከማስፈን ጋር ተያይዞ በተለይ ወንጀል ፈፅመው የተሸሸጉ ተጠርጣሪዎችን ወደ ህግ በማቅረብ በኩል ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ አንስተዋል ሌሎች በዚህኛዉ እቅድ አፈፃፀም የተጀማመሩ ተግባራት በቀጣዩ እቅድ ተካተዉ እንደሚከናወኑና ከፍትህ አካላት ጋር ያለዉ ቅንጅታዊ አሰራርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

 

በመጨረሻም በእቅድ አፈፃፀም ግምገማዉ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ከመጡ አካላት ጥያቄዎችና ሀሳቦች የተንሸራሸሩ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎች ተገቢዉን ማብራሪያና ምላሽ በመስጠት ግምገማዉ ተጠናቋል፡፡     


###

_X3A4741.JPG  _X3A4762.JPG