Search

ተቋሙ ጳጉሜ 5 ቀን 2011 ዓ.ም የሚከበረውን አገር አቀፍ የፍትህ ቀን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ

Published: 156 days ago

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፤ በፍትህ ተቋማት አዘጋጅነት “እኔ ለሕግ ተገዥ ነኝ”! በሚል መሪ ቃል ጳጉሜ 5 ቀን 2011 ዓ.ም የሚከበረውን አገር አቀፍ የፍትህ ቀን አስመልክቶ፤ ለመንግስትና ለግል ሚዲያዎች በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

 

መግለጫውን የሰጡት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱኑ እንደተናገሩት፤ የፍትሕ ቀንን ማክበር ያስፈለገበት ዋነኛው ምክኒያት፡- ባህሉን ስናከብር በአገራችን በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ የተጀመረው ለውጥ፤ የዘርፉን ተስፋ ያለመለመ ቢሆንም አሁንም ያሉብንን ተግዳሮቶች ለመለየት የሚያግዘን በመሆኑ፤ እንዲሁም ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የምትሆን በነፃነት፣ በፍትህ ተምሳሌትነት እና በእኩልነት ላይ የተመሠረተች ዴሞክራሲያዊት አገር ለመገንባት ፤ አዳዲስ አሰራሮችን፣ የሕግ ማህቀፎችን በማሻሻል አንፀባራቂ የለውጥ ድሎች በዘላቂነት በማረጋገጥ፤የትናንት የፍትህ ማነቆዎቻችን በማስወገድ፣ የዛሬ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ለቀጣይ ትውልድ የሚሆን ጽኑ መሰረት ያለው ትሩፋት መኖርን ለማመላከት ነው ብለዋል፡፡

 

ለዚህም ተግባር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እንዲጎላ ለማስቻል እና ፣በፍትህ ሥርዓቱ የሕግ የበላይነትን በማስከበር አገራዊ ለውጡ ስር ሰዶ መጪው ጊዜ ብሩህ እንዲሆን ለአንድ አገር ህልውናና ፤ለህብረተሰቡ ቀጣይ ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ወሳኝ ከመሆኑም ባሻገር የዴሞክራሲ ባህል እንዲያብብ፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን እና ሁሉን አቀፍ መሻሻሎች እውን እንዲሆኑ ለማስቻል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

 

ከዚህም ጋር ተያይዞ የፍትህ ተቋማት የተጣለባቸውን አገራዊ ተልዕኮ በመወጣት ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ዘመናዊ የሆነ የፍትህ አስተዳደር ለመገንባት ከህብረተሰቡ ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጎልበት፣ የህዝብን የነቃ ተሳትፎ በመጠቀም ዋስትና ያለው ፍትህ መገንባት የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ፤ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ለመግባበት ይህን ቀን ማክበር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝተዋል ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

 

በሀገራችን የተጀመረውን ለውጥ ለማሳለጥ ኅብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ሰፊ የውይይት መድረኮች በማዘጋጀት የሚታዩ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ በማጠንከር ደካማ ጎኖችን ደግሞ በማሻሻል የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ፤ በሀገራችን ሰላምና ዲሞክራሲ ማስፈን የበአሉ ዋና አላማ ው ሲሉም አቶ ዝናቡ በመግለጫቸው አብራርተዋል፡፡


ጳጉሜ 5 ቀን 2011 ዓ.ም በተለየ መልዕኩ የሚከበረው የፍትሕ ቀን በዓል፤ የፍትህ አካላት የሕዝብ አመኔታ ለማግኘት የሚያስችላቸውን ግብዓቶች ከሕዝቡ ለማሰባሰብ፣ ሕብረተሰቡ በፍትህ ሥርዓቱ ሂደት አጋርና ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን የሚያስችል መነሳሳት መፍጠር እና ሌሎች መሰል ተልዕኮዎችን ያነገበ መሆኑን በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

 

በዓሉ በፍትህ ስርዓቱ የታዩ ለውጦችና ያጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም በቀጣይ ያሉ ተልዕኮዎችን የሚገልጽ ስነድ ተዘጋጅቶ በ9ኙ ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ከህብረተሰቡና ከባለድርሻ አካላት፤ከዞን እስከ ወረዳ ድረስ የዉይይት መደረኮች ተዘጋጅተው ውይይት የሚደረግ ሲሆን እንዲሁም በተለያዩ አውደ ርዕዮችና የኪነ-ጥነብ ስራዎችን በማካተት ለህብረተሰቡ አስተማሪና አዝናኝ ዝግጅቶች የሚቀርቡ ሲሆን ጳጉሜ 5/2011 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት፣ ጥሪ የሚደረግላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችና ከክልል የሚመጡ እንግዶች በተገኙበት የመዝጊያና የምስጋና ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡

 

በፕሮግራሙ ላይም ለሀገራዊ አንድነት ለሰላምና ለፍትህ ሥርዓቱ መጎልበት አስዋጽኦ ያበረከቱ ግለሰቦችና ድርጅቶች የዕወቅና ሽልማት የሚሰጥ ሲሆን ፣ሌሎች አስተማሪና የመዝናኛ ፕሮግራሞችም እንደሚኖሩ ተገልጿል፡፡


በመጨረሻም አቶ ዝናቡ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ መሪ ቃሎች የሚከበረው ይህ በዓል ዘንድሮም ለ9ኛ ጊዜ “እኔ ለሕግ ተገዥ ነኝ”! በሚል መሪ ቃል በልዩ ሁኔታ ለሚከበረው በአል መሳካት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡


###

68565037_2421177244643012_5306094479713763328_o.jpg  69498978_2421177287976341_3822264423762886656_n.jpg