Search

በፍትህ ወር አከባበር ዙሪያ የፍትህ ዘርፍ አመራሮች ውይይት አካሄዱ

Published: 154 days ago

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ከክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አመራረቶች ጋር ነሃሴ 16 ቀን 2011 ዓ.ም ፍትህ እና ለውጥ በኢትዮጵያ በሚል የውይይት መነሻ ሰነድ ቀርቦ የፍትህ ወር አከባበር በተመለከተ ውይይት አካሄደ፡፡

 

ክቡር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ በውይይት መድረኩ እንደተናገሩት በህዝብ ዘንድ አመኔታ ያገኙ፣ ጠንከራ የዲሞክራሲና የፍትህ ተቋማት አለመኖር፣ የዲሞክራሲ ምህዳሩ መጥበብ፣ የፖለቲካና የሲቪል ነፃነቶች መሸርሸር ከለውጡ በፊት የነበሩ ተግዳሮቶች እና የፍትህ ጥያቄዎች ለውጡን አስፈላጊ እንዳደረጉት ጠቁመው፣ በለውጥ ዋዜማ ማህበረሰባዊ ብሶቶች፣ የዜጎችን ሰብአዊ መብት ከማስጠበቅ አንጻር ይታዩ ጉድለቶች ለህዝባዊ ቁጣ መንስኤ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

 

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ አያይዘውም በፍትህ ሥርዓቱ ቀልጣፋ፣ ፍትሐዊ፣ ተደራሽ እና ውጤታማ የሆነ በግልፅነትና ተጠያቂነት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት ለመስጠት የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ዋነኛው የለውጡ ማጠንጠኛ ማዕከል በማድረግ ከለውጡ በፊት እና በድህረ ለውጥ የተሰሩ ስራዎችን፣ የነበሩ ተግዳሮቶችን የጠቀሱ ሲሆን በቀጣይ በፍትህ ዘርፉ ሊሰሩ የሚገባቸውን ተግባራት በዝርዘር ተናግረዋል፡፡

 

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ በበኩላቸው በአገራችን የሚከበረው የፍትህ ወር በለውጡ ምዕራፍ ውስጥ ሆነን የምናከብረው በመሆኑ በዓሉን የተለየ እንደሚያደርገው ተናግረው የፍትህ አካለት ነጻና ገለልተኛ በመሆን ህብረተሰቡን ባሳተፍ መልኩ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል


###

69506486_2424532880974115_3986648786574245888_n.jpg