Search

የፍትህ ቀን በዓል በተለያዩ መርሃ-ግብሮች ተከብሮ ዋለ

Published: 136 days ago

የዘንድሮው የፍህ ቀን “ለህግ ተገዢ ነኝ!” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ-ግብሮች ጳጉሜ 05/2011 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በድምቀት ተከብሯል፡፡

 

በበዓሉ አከባበር የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ማለትም የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሐይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህበራትና የፖለቲካ ፓርቲ ተወካየች እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ከአዲስ አበባ ከተማና ዙርያዋ የተጋበዙ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

 

በዕለቱ በተላለፈው መልዕክት የፍትህ ስርዓቱን ወደተሸለ ደረጃ ለማድረስና የሕግ የበላይነትን ለማሰጠበቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ መላውን ህብረተሰብ የሳተፈ መሆን እንዳለበት የተጠቆመ ሲሆን ፍትህ የነገሰባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁሉም የሚጠበቅበትን እንዲወጣም ጥሪ ቀርቧል፡፡


###

ፕሬዚዳንት-ሳህለወርቅ-ዘውዴ.jpg