Search

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና በአሜሪካው ተራድዖ ድርጅት (USAID) የፍትህ ፕሮጀክት ለዐቃብያነ ህጎች እና የህግ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

Published: 106 days ago

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና በአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (USAID) የፍትህ ፕሮጀክት ከ15 የተለያዩ የመንግሰት ተቋማት ለተውጣጡ የህግ ባለሙያዎች እና ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፍትሐብሔር ፍትሕ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት፣ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳሬክቶሬት እንዲሁም ከሁሉም ምድብ ጽ/ቤቶች የድሬድዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጨምሮ ለተውጣጡ ዐቃቢ ህጎች በአለም አቀፍ የውል ዝግጅት እና ድርድር እንዲሁም በአለም አቀፍ የግልግ ዳኝነት መርሆዎች እና ክህሎቶች ላይ በ2 ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

 

ስልጠናው ከውጪ ሀገር እና ከሀገር ውስጥ በመጡ በዘርፉ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ከመስከረም 19 እስከ 21 እና ከመስከረም 26 እስከ 28 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በ2 ዙር በቢሾፍቱ ከተማ አሻም አፍሪካ ሎጅ የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው ላይም 50 የሚሆኑ የህግ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

 

ስልጠናው አቅምን በማሳደግ ረገድ ተጨማሪ አቅም የፈጠረላቸው መሆኑን ሰልጣኞቹ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን በመድረኩ ላይም ሰፊ የልምድ ልውውጥ መደረጉን አውስተዋል፡፡


###

71948271_2517475695013166_1411974510059454464_o.jpg