Search

በሁለተኛው የሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሐ ግብር አፈጻጸም ዙሪያ ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አመራሮች ጋር ውይይት ተደረገ

Published: 102 days ago

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብሔራዊ የሰብአዊ መብት ድርጊት መርኃ ግብር ጽ/ቤት በሁለተኛው ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሐ ግብር አፈጻጸም ዙሪያ ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አመራሮችና ከተለያዩ ከክልሉ መንግስት ቢሮዎች ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋር በክልሉ ውቅሮ ከተማ ጥቅምት 3 እና 4/02/2012 ዓ.ም ውይይት አደረገ።

 

በውይይት መድረኩ የድርጊት መርሐ ግብሩ ምንነት ይዘት እና አፈጻጸም ስልት ዙሪያ አጭር ገለጻ የተደረገ ሲሆን የ2012ዓ.ም በጀት ዓመት የሁለተኛው ድርጊት መርሐ ግብር የመጨረሻ ትግበራ ዘመን እንደመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲተገበሩ በሚያስችላ መልኩ በብሔራዊ አስተባባሪ ቦርዱ በተለዩ ተግባራት አፈጻጸም ዙሪያም ውይይት ተደርጓል።

 

የክልሉ ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴም በበኩሉ ሁሉም በክልሉ የሚገኙና በድርጊት መርሐ ግብሩ ሃላፊነት የተሰጣቸው ተቋማት ሁሉ ስራዎችን በተገቢው እንዲወጡ አሳስቦ ይህንንም በየጊዜው በሚያድርግባቸው የክትትል እና ግምገማ ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ እንደሚከታተል አስታውቋል።

 

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የክልሉ መንግስት የድርጊት መርሐ ግብሩን እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ልዩ ትኩረት የሚሰጣቸውን ተግባራት ለመፈጸም ቁርጠኝነት ያላቸው መሆኑን እና ለተፈጻሚነቱም ከብሔራዊ አስተባባሪ ጽ/ቤቱ ጋር በጋራ ለመንቀሳቀስ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸው የውይይት መድረኩ ተጠናቋል።


###

72836923_2528219897272079_1644626038010937344_o.jpg