Search

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዩ የፍትህና የሕግ ምርምር እና ስልጠና ኢንስቲትዩት ጎበኙ

Published: 96 days ago

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ እና የመንግስት ኃላፊዎች በተገኙበተ አዲስ የተገነባውን የፌዴራል የፍትህና የሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩትን ማዕከልን በዛሬው እለት ጉብኝት አካሄዱ፡፡

 

የፌዴራል የፍትህና የሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘካሪያስ ኤርኮላ የጉብኙትን ዋና አላማ አስመልክተው እንደተናገሩት የስልጠና ማዕከሉ በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ የተገነባና ስራ የጀመረ መሆኑን ጠቁመው የተቋሙ የበላይ አመራሮች፣ ሚኒስትሮችና የአውሮፓ ህብረት ተወካይ ህንጻው ያለበትን ደረጃ አይተው ቀጣይ ስራዎችን ለማጠናቀቅ መደገፍ ያለባቸውን እንዲደግፉ ለማድረግ መሆን ተናግረዋል፡፡

 

ኃላፊው አያይዘውም የስልጠና ተቋሙ አራት ዋና ዋና የትኩረት መስኮች ያሉት ሲሆን ለፍትህ አካለት ለዳኞች፣ ለዐቃቤ ሕጎች፣ ለፖሊስ አባላት የቅድመ ስራ እና የስራ ላይ ስልጠና መስጠት እና ከዩኒቨርሲቲ አዲስ ለሚመረቁ የሕግ ተማሪዎች ከ8 ወር እስከ 1 አመት የሚቆይ ስልጠና መስጠት፣ ክፍያን መሰረት በማድረግ ልዩ ስልጠና ድርጅቶች መስጠት፣ በሕጎችና ፍትህ ሥርዓቱ ያሉ ችግሮችን ጥናትና ምርምር በማድረግ የለውጥ ሪፎርሙን ማጠናከር እና የፍትህ እና የሕግ መረጃ ማዕከል ማደረጀትና መረጃን ተደራሽነት በማጠናከር በተግባር የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ይረዳል ብለዋል፡፡

 

አቶ ዘካሪያስ ኤርኮላ አክለውም ኢንስትቲዩቱ በፍትህና በህግ ጉዳዮች ጥናትና ምርምርን እንዲያደርግ፣ የፍትህ አካላት አመራሮችንና ባለሙዎች በእውቀትና በክህሎት ለማሳደግ አለማ ያደረገ ሲሆን ተቋሙ የሰው ሀይል እጥረት፣ ውስን ተመራማሪዎች መኖር እና የደመወዝ መጠን ሳቢ አለመሆን ብሎም የግብአት እጥረት የተቋሙ ችግሮች መሆናቸውን ጠቁመው በቀጣይ የግብዓት እና መሰል ችግሮች እንደሚሟሉ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡


###

74238223_2545815608845841_1021297314083373056_o.jpg