Search

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይንም ንብረትን ህጋዊ አሰመስሎ ማቅረብን መከላከልና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ለመካከለኛ አመራሩ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል

Published: 93 days ago

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይንም ንብረትን ህጋዊ አሰመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዝብ የመደገፍ ወንጀልን እንዲሁም ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰቶችን መከላከል በምያስችሉ አሰራሮች ዙሪያ ለመካከለኛ አመራሩ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

 

ስልጠናው እየተሰጠ ያለው ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተቋም ለተወጣጡ መካከለኛ አመራሮች ሲሆን ለሁለት ቀናት እንደሚቆይም ታውቋል፡፡

 

ስልጠናው በወንጀል ደርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይንም ንብረትን ህጋዊ አሰመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዝብ የመደገፍ ወንጀልን እንዲሁም ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰቶችን ከመከላከል አንፃር አለማቀፍ የህግ ማዕቀፎች ቀኝት፣ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይንም ንብረትን ህጋዊ አሰመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዝብ የመደገፍ ወንጀልን እንዲሁም ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰቶችን የመከላከል እንቅስቃሴ በኢትዮጵያና በአለምቀፍ ተሞክሮዎች ዙሪያ እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ርዕሶች ላይ ትኩረት ያደረገ እንደንሆነም መረዳት ችለናል፡፡

 

በሥልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ እንደተናገሩት በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይንም ንብረትን ህጋዊ አሰመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዝብ የመደገፍ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ የሚሰሩ አካላትን ግንዛቤ በማሳደግ ወቅቱ የሚጠይቀውን የወንጀል መከላከልና የመቆጣጠር ስትራቴጂ የመዘርጋት ተግባር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል በማለትም ተናግረዋል ፡፡

 

በማያያዝም ወንጀለኞችን በእስራት ከማስቀጣት ጎን ለጎን በወንጀሉ መፈፀም የሚገኘውን ገንዘብና ንብረት እንዲወረስ በማድረግ እንዲሁም በሕግ አግባብ በማሳገድና በማስተዳደር የወንጀለኞችን አቅም ማሳጣትና የህብረተሰቡን ከወንጀል የመጠበቅ መብት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡

 

በኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተቋም የሕግ ማርቀቅና ማስረጽ ዳይሬክቶሬት ም/ዳይሬክተር የሆኑት አቶ እንዳልካቸው ወርቁ ፕሮግረሙን በማስመልከት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቀው ከአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ፕሮግራሙ ጋር ተያይዞ በቀጣይ በተለየዩ ምዕራፎች ተከፍሎ ለዐቃቢያነ ሕጎች፣ ለፖሊስ አባላትና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ተከታታይ የሆነ ስልጠና እንደሚሰጥ የገለጹ ሲሆን ወንጀሉን ከመከላከል አንፃር ከፍተኛ አቅም ይፈጥራልም ብለዋል፡፡

ም/ዳይሬክተሩ አይይዘውም የአቀም ማጎልበቻ ሥልጠና ፕሮግራሙ የሚከናወነው በኢትዮጵያ የዴኒማርክ ኢምባሲ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2019 እሰከ 2022 ባለው ጊዜው ውስጥ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው ስልጠናው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና በጣና ኮፐንሃገን አለም አቀፍ የምክር አገልግሎት ድርጅት አማካኝነት በጋራ የሚሰጥ እንደሆነም ጠቁመዎል፡፡

 

ስልጠናውን ለተሳታፊዎች እየሰጡ ያሉት Mr. ቻርለስ ጎርደማ ሲሆኑ በተደራጁና አለም አቀፍ ይዘት ባላቸው ወንጀሎች እንዲሁም በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይንም ንብረትን ህጋዊ አሰመስሎ ማቅረብን በመከላከሉ ሂደት በተለይ ከአፍሪካ ምጣኔ ሀብት ጋር በተያያዘ ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀሎችን መከላከል በሚያስችሉ አሰራሮች ዙሪያ ከፍተኛ የሆነ የማማከር ልምድና በዘርፉ የተለያዩ ጥናቶችን ያደረጉ ሲሆኑ እሳቸውም እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይንም ንብረትን ህጋዊ አሰመስሎ ማቅረብን በመከላከል ረገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሻለ አፈፃፀም እያስመዘገበች የመጣች ሀገር በመሆኗ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ሥልጠና ፕሮግራሙ የተሸል አቅም ይፈጥራል ብለዋል፡፡

 

በሌላ በኩል ለተሳታፊዎቹ ስልጠና በሰጡበት ወቅት በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይንም ንብረትን ህጋዊ አሰመስሎ ማቅረብና ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰቶችን ከመከላከል አንፃር ኢትዮጵያ በቅርቡ እያስመዘገበች በመጣችው ውጤት መሠረት ከብላክ ሊስት ደረጃ ሰሞኑን መውጣቷን የጠቆሙት ዐቃቤ ሕግ አቶ ቢንያም ሽፈራው የተመዘገበው ውጤት የሚያበረታታ በመሆኑ የበለጠ ለመስራት ያስችላልም ብለዋል፡፡

 

ስልጠናው በነገው እለትም በተለያዩ ርዕሶች የሚቀጥል መሆኑ ታውቋል፡፡


###

73160279_2548123025281766_8965569597029744640_o.jpg