Search

ሰኔ 15/2011 ዓ.ም በከፍተኛ አመራሮች ላይ በተፈጸመው የግድያ ወንጀል የምርመራ ውጤት ላይ መግለጫ ተሰጠ

Published: 144 days ago

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና በአዲስ አበባ ከተማ በመከላከያ ኢታመጆር ሹም እና በቀድሞው ጀኔራል ላይ የተፈጸመውን ወንጀል አስመልክቶ ክስ ለመመስረት ባጠናቀራቸው የምርመራ ውጤቶች ላይ ዛሬ በተቋሙ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡

 

ወንጀሉ በአማራ ክልል የደህንነት ቢሮ ኃላፊ በነበሩት በብርጋዴል ጀነራል አሳምነው ጽጌ መሪነት መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን ድርጊቱን ለመፈጸምም ከሚያዚያ 2011 ዓ.ም ጀምሮ የተለያ ዝግጅቶች ሲደረጉ የቆዩ እንደቆዩም ተገልቷጧል፡፡

 

በዚህም በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ላይ በአንዳንድ አክቲቪስቶች አማካኝነት ጀነራል አሳምነው ጽጌ የተበደለ በማስመሰል በአመራሮቹ ላይ የስማ ጥፋት ዘመቻ የነበረ ሲሆን ለወንጀሉ ማስፈጸሚያነትም ከመከላከያ ሰራዊት አባልነታቸው በራሳቸው ፍቃድ የለቀቁትንና፤ በዲሲቲሊን ምክኒያት በወንጀል ሳይከሰሱ የተሰናበቱትን አባላትን፤ የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት በተልዕኮና በግድያ ወንጀሎች ላይ እንዲሳተፉ መደረጉን ተገልጧል፡፡

 

በመግለጫው ላይ እንደተመላከተው በባህር ዳር በ55 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ለመመስረት ዝግጅት የተደረገ ሲሆን በአዲስ አበባ ደግሞ በ13 ሰዎች ላይ ክስ ለመመስረት ዝግጅት መደረጉን ክቡር ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ አቶ ብርሀኑ ጸጋዪ ገልጸዋል፡፡


###

75481675_2588824357878299_3643387690243588096_o.jpg