Search

ከወንጀል ምርመራና ከክስ አመሰራረት ጋር ተያይዞ ስልጠና እየተሰጠ ነው

Published: 134 days ago

በኢ.ፊ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ለሚገኙ አቃብያነ ህጎች ከወንጀል ምርመራና ከክስ አመሰራረት ጋር ተያይዞ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ልደታ አዳራሽ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

 

በስልጠና መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በህግ ማስፈጸም ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተወካይ የሆኑት፤ አቶ ብርሃኑ ወንድምአገኝ እንደተናገሩት የዐቃቤ ህግን የማስረጃና የክርክር ክህሎት ለማዳበር ልምድ መለዋወጥ ለስራው ስኬት አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ የስልጠና መድረኩን ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

 

ስልጠናው በወንጀል ምርመራ የዐቃቤ ህግ ሚና ምንድን ነው?ዐቃቤ ህግ የወንጀል ምርመራን እንዴት መምራት ይችላል? የወንጀል ምርመራ አላማ ተግባርና መርሆ ምንድን ነው?የወንጀል ምርመራ በማን ይሰራል ምን እውቀትና ክህሎት ይጠይቃል? በተግባር የሚታዩ ክፍተቶችስ ምንድን ናቸው እንዴትስ ሊቀረፉ ይችላሉ? እንዲሁም ዐቃቤ ህግነት ምንድን ነው፣ በኢትዮጵያ የዐቃቤ ህግነት ታሪክ በሚሉ አበይት ጉዳዮች ላይ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የጉለሌ ምድብ ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ይግረማቸው ከፈለኝ ከተቋሙ ከተለያዩ ክፍሎች ለተውጣጡ 50 ለሚሆኑ ዐቃቤ ህጎች እየተሠጠ ይገኛል፡፡

 

በነዚህና በመሰል ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል፡፡


###

74910733_2600042543423147_3210525578889265152_o.jpg