Search

የድንበር አጠቃቀምን በማዘመን ተጠቃሚነትን ማሳደግ እንደሚቻል ተገለጸ

Published: 125 days ago

በኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሚመራው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ተከላካይ ግብረ ኃይልና ለጸጥታ አካላት በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ባህሪያትና የተቀናጀ የድንበር አስተዳደር ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

 

በአገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አሳሳቢ እየሆነ የመጣው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ዘርፈ ብዙ ጉዳቶችን እያስከተለ እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን ድህነት፣ ስራአጥነትና ክብርን የሚነኩ ድርጊቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው ተብሏል ፡፡

 

በመሆኑም ድርጊቱን ለመከላከል ግብረ ኃይሉ ቅንጅታዊ ያለውና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስራ መስራት እንዳለበት ተጠቅሷል፡፡

 

ስልጠናውን የሰጡት የIOM ባልደባ የሆኑት አቶ ማርሴሎኒ ድንበርን በቅንጅትና በተገቢው መንገድ ማስተዳደር የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ከማስጠበቁም በላይ አላስፈላጊ ከሆኑ ጉዳቶች ለመጠበቅ ይረዳል በተጨማሪም በድንበር በኩል የምናገኘውን ጥቅም ለማሳደግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

 

በመሆኑም የእርስ በእርስ፣ ከሌሎች ተቋማት እና ከሀገር ውጪ ካሉ ሀገራት ጋር በቅንጅት መስራቱ ሊሰመርበት ይገባል ብለዋል፡፡ ስልጠናው እስከ ህዳር 19 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ይሆናል ፡፡


###

75380205_2623274174433317_3363025350580764672_o.jpg