Search

ተቋሙ በበጀት ዓመቱ የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ግምገማዊ ውይይት እያካሄደ ይገኛል

Published: 124 days ago

የኢ.ፌ..ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የ2012 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን አስመልክቶ ዛሬ በካፒታል ሆቴል ከተቋሙ ከፍተኛና መካካለኛ አመራሮች ጋር እየገመገመ ነው፡፡

 

በውይይት መድረኩም እንደሀገር የተጀመረውን ሁለንተናዊ ለውጥ ለማስቀጠል ከተወሰደው ሀገራዊ ኃላፊነት ጋር በማቀናጀት በሰብአዊ መብቶች አያያዝ በሙስና ወንጀሎች፣ በልዩ ልዩና ድንበር ተሻጋሪ እንዲሁም ከሌሎች ወንጀሎች ጋር ተያይዞ በነበሩ አፈጻጸሞች ዙሪያ ሪፖርቶች እየቀረቡ ሲሆን በቀጣይም በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት ከተደረገበት በኃላ ቀጣይ አቅጣጫዎች ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡ በተጨማሪም የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የ10 ዓመት ረቂቅ ስትራቴጂ ላይም ውይይት እንደሚያደርግም ይጠበቃል።

 

የውይይት መድረክ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል፡፡


###

77230688_2624740300953371_8092541838268825600_o.jpg